loading
0%PROJECT – III ሶስተኛው፤ መርሃ፡ ግብር፡፡
አንኮበር፡ ወረዳ፤ እመ፡ምህረት ተራራ አጠገብ፤ ጠመጅ፡ ምድር፡ ላይ፤ ለቦለድ፡ባለወልድ፤ ለሲና፡ ሚካኤል፡ እና፡ ደረፎ፡ ማርያም፤ ላሉ፡
አጎራባች፤ ማኅበረሰብ፡ ህጻናት፡ ማዕከል፡ እንዲሆን፡ ታስቦ፡ የተሰራ፡ ት/ቤት፡፡
Ankober Woreda; Western foot of Eme Mihiret mountain at Te'mej Midir;
For Qundi Giorgis, and as centre for surrounding communities; (Boled Balewold; Sina Mikael & Derefo Mariam):
ታሕሣስ፡ 2002 ዓ/ም፤ የቁንዲ / እመ፡ምህረት፡ ተማሪዎችን፡ የመጀመርያው፡ ጉብኝት፡ ባካሄድንበት፡ ወቀት፤ ፡፡ ተማሪዎቹ፡ መማርያ፡ ክፍል፡ ውስጥ፡ እና፡ ውጪ፤ መሃል፡ ከቆሙት፤ የፈብ፡ አባላት፤ አቶ፡ አክሊሉ፡ ዘውዴ፤ አቶ፡ ጌታሁን፡ ደምሴ፡ እና፡ ፡ ዘላለም፡ እውነቱ፡ ይታያሉ፡፡ December 2009; Qundi / EmeMihiret students in / outside their class room. Amongst them, FB members; Alilu Zewde etal.
ይህ፡ የአንኮበር፡ ገበሬ፡ ባህላዊ፡ ባለጭስ፡ ማውጫ፡ መኖርያ፡ ቤት፤ ከቁንዲው፡ ት/ቤት፤ የተሸለ፡ገጽታ፡ ነበረው፡፡ The school at Qundi was not as attractive as the above traditional oval chimney fitted, Ankober’s farmermer’s house.
ሌላው፡ በአንኮበር፡ ወረዳ፡ ውስጥ፤ የፈለገ፡ ብርሃን፡ ማኅበር፡ አስተዋጽኦ፡ የሚያስፈልገው፤ በአንኮበር፡ እና፡ ሚጣቅ፡ አማኑኤል፡ መሃል፤ ለሚገኘው፡ የሲና፡ ሚካኤል፡ ነዋሪዎች፡ ህጻናት፡ ነበር፡፡ የሲና፡ ሚካኤል፡ አካባቢ፡ ህጻና፤ ጉልበታቸው፡ ሲጠነክር፤ ከሚኖሩበት፤ ከአንኮበር፡ እና፡ ሚጣቅ፡ መሃል፤ ያለውን፡ የደረፎ፡ ማርያም፡ ተራራን፤ በመውጣት/በመውረድ፤ ተራራው፡ አናት፡ ላይ፡ ባለው፡ የመ/ደ/ት/ቤት፡ ለመማር፡ ይሄዳሉ፡፡ በጉብኝታችን፡ ወቅት፡ ለት/ቤቱ፤ የጽ/መሣርያዎችን፡ እርዳታ፡ አድርገን፡ ነበር፡፡ ት/ቤቱን፡ እንደ፡ ቁንዲው/እመ፡ምህረቱ፤ ለማሰራት፡ አቅም፡ ስላነሰን፡ አቆይተነዋል፡፡
The 2nd FB support should have been for Sina Mikael area, half way from Ankober and Mitaq Ammanuel; on Easter side of Derefo Mariam Mountain. Sina Mikael students travel each day; up/down hill to top of Derefo Mountain to attend primary school at
Derefo Mariam School. We gave a token present/stationeries to the school, during our preliminary assessment visit of the area and decided to postpone our wish to also build a school for Sina Mikael kids; since we couldn't do it that time because of shortage of resources. Nevertheless; they are included in our annual stationary and scholastic award scheme benefits / events each year.
ከደረፎ፡ ተራራዎች፤ ተፋሰስ፡ በስተምዕራብ፡ በጨው፡ በሌ፡ እና፡ ዳቦ፡ በሌ፡ ወንዞች፡ መሃል፤ ደኑ፡ ውስጥ፤ ለው፡ የአቦ፡ ገዳም፡ ሲሆን፤ ባሻገሩ፤ የሚጣቅ፡ አማኤል፤ ቤተ፡ ክርስቲያን፤ እና፡ አንገት፡ መውግያ፡ መንደር፡ ይገኛሉ፡፡The weastern watershed of Derefo mountain range overlooks Mitaq Amanuel monastry. Pic 2, on top of Derefo, Ato Ejigayehu (D/Education head Ankober Woreda) with Ato Zelalem Ewnetu of WFP, and Ato Aklilu Zewde; former Dean of St. Yared Music School. Pic. 3 Ato zelalem Ewnetu and the late Ato Getahun Demissie; handed our token stationary support on behalf of all FB.
ፎቶ 1፡ በሶስተኛው፡ ጉብኝታችን፡ ወቅት፤ በውጭ፡ አገር፡ ከሚኖሩት፡ አባሎቻችን፤ አንዱ፡ ከነበረው፤ ፕሮፌሰር፡አሰፋ፡እንደሻው፤እና፡ሌሎች፤አባላት፤ጋር፤ እቦታው፡በመሄድ፤ ት/ቤቱ፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡ ውብ፡መስክ፡ላይ፡ ከተማሪዎቹ፤ እና፡ መምህራኖቻቸው፡ጋር፤ መታሰብያ፤ ፎቶ፡ተነሳን፡፡ ፎቶ 1፡ ከጀርባችን፤ እና ፎቶ 2፡ ላይ፤ ጥቅጥቅ፡ ያለው፡ የባህር፡ዛፍ፡ደን፡ የለበሰው፡ ተራራማ፡ሰንሰለት፤ ቦለድ፡ባለወልድ፤ ደረፎ፡ማርያም፡ እና፡ ሲና፡ሚካኤል፡ የሚገኙበት፡ተፋሰስ፡ነው፡፡
Pic 1: FB Ethiopia members 3rd visit with a member living abroad: spora including Prof. Assefa E ndeshaw. Pic. 2: Boled Balewold; and Derefo Mariam Pr. Schools are on top of the watershed while Sina Mikael is half way facing East to Ankober.
ቀጥለንም፤ ህዳር፡ 10 ቀን፤ 2004 ዓ/ም፤ እመ፡ ምህረተር፡አጠገብ፡ ላሉት ለቁንዲ፡ ጊዮርጊስ፡ እና፤ ጠመጅ፡ ምድር፡ ህጻናት፤ አዲስ፡ ት/ቤትን፡ ለመስራት፤ ከአካባቢው፡ ማኅበረስብ፡ እና፡ ከአንኮበር፡ ወረዳ፡ ት/ጽቤት፡ ጋር፤ የሶስትዮሽ፡ የጋራ፡ ስምምነት፤ ተፈራረምን፡፡ አቶ፡ ዳኛቸው፡ ወንድሙ፡ እና፡ ምክትሉ፡ አቶ፡ እጅጋየሁ፡ ተክሌ፤ በጣም፡ ተባባሪ፡ የት/ቢሮው፡ ሃላፊዎች፡ ነበሩ፡፡ ት/ቤቱን፡ እውን፡ ልናደርግ፡ የቻልነው፡ በነሱም፡ ከፍተኛ፡ ትብብር፡ ነው፡፡
In November 2011, Felege Birhan Association signed a tripartite agreement with Ankober Woreda Education office and representatives of T'emej Midr / Qundi Giorgis communities at Emme Miheret to realize an MOE standard school proper .
በት/ቤቱ፡ ግንባታ፡ ሂደት፡ ወቅት፡ በየጊዜው፡ በመመላለስ፡ ለተለያዩ፡ ስራ፡ ተቋራጮች፡ የሰጠነውን፡ ስራ፡ በመመላለስ፡ እንገመግም፡ ነበር፡፡
ፎቶ፡ 1፡ ከጀርባ/ሩቅ፡ የሚታየው፤ የመማርያ፡ ክፍሎቹ፡ እና፡ የመምህራን፡ ቢሮ፡ ስራ፡ ጅምር፡ ሲሆን፤ ፊት፡ ለፊት፡ ለመጸዳጃ፡ ቤቶቹ፡ ስራ፡ መሰረት፡ ሲጣል፡፡
ፎቶ፡ 2፡ ከወንድሜ፡ መላኩ፡ በዛ፡ ጋር፡ እጅግ፡ ብርዳማ / ጉማማ፡ በነበረበት፡ ቀን፤ ባለ 6 ክፍሉን፡ መጻዳጃ፡ ቤት፡ ስራ፡ ሂደት፡ ስንገመግም፡፡ ጉሙ፡ምን፡ያህል፤
የምናየውን፡የእመ፡ምሀወረት፡ተራራ፡እንደሸፈነው፡እናያለን፡፡ በአንድ፡የመስቀል፡በዓል፡ቀን፡ከማህበረ፡ሰቡ፡ጋር፡ወጥቼው፡ሀይቅ፡እንዳለበት፡አረጋግጫለሁ፡፡
4/
ከአንድ፡ዓመት፤ከስምንት፡ወራት፡ጥረት፡ በኋላ፤ ለአንኮበር፡እመ፡ምህረት፡ህዝብ/ተማሪዎች፤ ዘመናዊ፡ት/ቤትን፡ እና፡ ንጹህ
የመጠጥ፡ውሃን፡ከት/ጽ/ቤቱ፡እና፡ማህበረሰቡ፡ጋር፡በመተባበር፤አሰርተን፡አስረከብን፡፡ ለዚህም፤እግዚአብሔርን፡ እናመሰግናለን፡፡
After about a year and eight months; we realized a school proper and clean drinking water to Ankober's Eme miheret and Qundi Giorgis Communities/Children. Pic: 3: የሥራ፡አመራር፡አባላት፤(ወ/ሮ፡ስንዱ፡ብሥራት፤ፕሮፌሰር፡አበራ፡ገይድ፤አቶ፡ ዘላለም፡እውነቱ) እና፡ታደሰ፡ተገኝ፤ በወረዳው፡ ት/ጽህፈት፡ በተወያየንበት፡እለት፡፡ በእለቱም፤የት/ቤቱን፡የመጠጥ፡ውሃ፡አቅርቦት፤በመረቅንበት፡ እለት፡፡ Board members: w/ro Sinedu Bisrat; Prof. Abera Geyid; Ato Zelalem Ewnetu and Tadesse Tegegne's visit and inauguration of the school's new water supply system.
5/
የት/ቤቱ፡የመጠጥ፡ውሃ፡አቅርቦት፡መርሃ፡ግብር፤ ለት/ቤቱ፡ብቻ፡ሳይሆን፤ ከወረዳው፡ አስተዳር፡ ጋር፡ በመተባር፤ ከት/ቤቱ፡በታች፤ ወደ፡ አንኮበር፡ ከተማ፤ ተፋሰስ፤ ላሉ፤ ሶስት/አራት፡ የገበሬ፤ ቀበሌ፡ መንደሮችም፤ ተስቦ፡ በየመንደራቸው፡ እንዲደርስ፡ ተደርጓል፡፡
The School's water supply system has also benefited down stream to 3 farmers communities;
by extending the over flow with pipe, in cooperation with the Woreda Water supply office .
Pic6: ማርያም ሆይ፤ አንቺ፡ብፅዕት፡ነሽ፤የምትመረጪ፤ በወርቃማው ጫማሽ፤ ውሻ፡ እምታጠጪ፡፡(ከድረ፡ገጽ፡የተገኘ)
ለት/ቤታችን፡ ብለን፡ ያሰራነው፡ የመጠጥ፡ ውሃ፡ አቅርቦት፤ እመ፡ምህረት፡ አጠገብ፤ ለጠመጅ፡ ምድር፡ እና፡ ከዝያም፡ በታች፡ ወደ፡ አንኮበር፡ ከተማ፡ ጎረቤላ፡ መውረጃው፡ ላይ፡ ላሉ፡ የገበሬ፡ መንደሮችም፡ ተስቦ፡ አገልግሎት፡ እየሰጠ፡ ስለሆነ፤ የታላቁ፡ ንጉሠ፡ነገሥታችን፤ ቀ/ኃ/ሥላሴን፡ በበጎ፡ ፈቃድ፡ አገራችንን፡ እና፤ መረዳት፡ ላለባቸው፡ ሁሉ፡ እንድንረዳ፤ የተዉልንን፤ አደራ፤ በቻልነው፡ መጠን፤ ስለተገበርን፡ ደስ፡ አለን ፡፡
We are proud to have done all we could, and lived true to the expectation of our beloved Emperor Haile Selassie: who wished all educated/able Ethiopians give free voluntary service to their country and people. The water supply is also being used by farming villages close to the school, and others down hill living towards Ankober town called Gorebela.
On this day; we proposed constructing an additional block of four class rooms, to get sufficient space for further upgrading of the school. The Education Office insisted that we first should deposit the money for construction in its bank account, and then finance by withdrawing from that account. We turned down this idea since for us it was an act of moving to corruption. Our future generation should also take care on such issues, and stay away from corrupt officials.
ATO ANTENEH YEMIRU; ATO KIBKAB MELISSE AND TADESSE TEGEGNE's STATIONARY DONATION DAY; ON BEHALF OF ALL FB MEMBERS.
DAY, KASSAYE BETRE; WORQNEH TESFAYE AND TADESSE TEGEGNE, INSTALLED SOLAR ELECTRIC POWER AND TV FOR THE SCHOOL / COMMUNITY:
DAY, ATO KIBRET SURAPHEL; MAMO H/KIRISTOS; WORQNEH TESFAYE AND TADESSE TEGEGNE VISITED THE CONTINUING USE OF THE SCHOOL'S NEWLY INSTALLED ELECTRICITY/EDUCATIONAL TV; AND DISCUSSED WITH THE STAFF:
DAY, ATO DAGNACHEWWONDIMU (Head; Ankober Woreda Education Office); AKALU SAHILU; TADELLE TEFERA AND TADESSE TEGEGNE VISITED THE SCHOOL AND DONATED STATIONARY ITEMS; AND SMALL CASH AWARDS AND CERTIFICATES TO BEST PERFORMING STUDENTS:
DAY, TADELE TEFERA AND I TRAVELLED TO OUR QUNDI GIORGIS SCHOOL; TOGETHER WITH SELAM VOCATIONAL CENTER'S PROFESSIONALS; WITH MODERN; MILK CHURNER; BEE HIVES; AND CROP THRESHER; TO DEMONSTRATE TO PARENTS OF OUR SCHOOL CHILDREN WHO MAKE A LIVING BY FARMING IN THE LOCALITY .
ይህን፡ ለአካባቢው፡ ገበሬዎች፡ እና፡ ለት/ቤታችን፡ መምህራን፡ እና፡ ተማሪዎቻችን፡ ባስተዋወቅንበት፡ ማግስት፡ ከአንኮበር፡ ወረዳ፡ ስልክ፡ ተደውሎልኝ፤ የመጨረሻ፡ ማስጠንቀቅያ፡ ተብሎ፡ ሁለተኛ፤ እንዳንደግም፡ ተነገረኝ፡፡ " አንተ፡ አንኮበር፡ የምትመላሰው፡ ህጻናት፡ ተማሪዎችን፡ እንረዳለን፡ በማለትህ፡ እንጂ፤ ገበሬዎችን፡ ልታሰባስብ፡ አይደለም" አለኝ፡፡ ይህም፡ የሆነው፤ እነ፡ አቶ፡ ዳኛቸው፡ እና፡ አቶ፡ እጅሀጋየሁ፡ ወደሌላ፡ ተዛውረው፡ አዲስ፡ ሹመኞች፡ ከመጡ፡ በኋላ፡ ነበር፡፡ እኔም፡ ለማስረዳት፡ ሞከርኩ፡፡ ሆኖም፡ ሁሉንም፡ በትእግስት፡ አሳለፍነው፡፡
DAY, SENAY AND ESSETE TADELLE TRAVELLED WITH THEIR DAD; TADELE TEFERA, AND I; TO VISIT FB'S ANKOBER QUNDI GIORGIS PRIMARY SCHOOL AND DONATE SCHOOL STATIONARY ITEMS TO THE STUDENTS:
ከጀርባችን፤ እመ፡ ምህረት፡ ተራራ፡ እና፤ ወፍ፡ ዋሻ፡ ደን፡፡ ደኑ፡ እንደ፡ ሰንሰለት፤ በደብረ፡ ሲና፡ አድርጎ፡ መንዝ፡ ይደርሳል፡፡
Emme Mihiret mountain covered with Wof Washa forest, that runs as a chain from Ankober to parts of Yifat, and Menz Gishe Awrajas.
የፈብ፡ አባላት፤ ከግራ፡ ወደ፡ ቀኝ፤ አቶ፡ ተስፉ፤ ታደሰ፡ ተገኝ፤
ጌታሁን፡ ደምሴ፡ እና፤ የጀነራል፡ዊንጌት፡ት/ቤት፡ጓደኛችን፤ ይትባረክ፡ዓለሙ፤
ቁንዲ፡ጊዮርጊስን፡ እና፡ ት/ቤታችንን፡ በጎበኘንበት፡ እለት፡፡
በዚህ፡እለት፤የአካባቢው፡ህዝብ፡ደመራን፡እመ፡ምህረት፡ተራራ፡ላይ፡ስለነበር፡የሚያከብረው፡ሌሎቹ፡ጓደኞቼ፡መውጣት፡ስለሰጉ፤እኔ፤ከህዝቡ፡ጋር፡ ተራራው፡ላይ፡ወጥቼ፤በፈብ፡አባላት፡ስም፡አከብርያለሁ፡፡ ተራራው፡ላይም፡ሐይቅ፡ አየሁ፡፡ እመቤታችንም፡እላዩ፡ላይ፡ለወራት፡ኖራለች፡ይባላል፡፡
የወረዳው፡ ትምህርት፡ ጽ/ቤት፡ ሃላፊ፡ አቶ፡ ዳኛቸው፡ ወንደሙ፡ ለመታሰብያ፡ ከተማሪዎቻችን፡ ጋር፡፡
13/
አቶ፡ ግሩም፤ ወ/ሚካኤል፡ በባለባታቸው፡ ወ/ሮ፡ ሥምረት፡ መላከ፡ ሕይወት፤ በልጆቻቸው፡ እና፡ በራሳቸውም፡ ስም፡ ፈለገ፡ ብርሃን፡ ማኅበር፤ በአንኮበር፡ እና፡ ተጉለት፡ ለሚያካሂዳቸው፡ የመ/ደ/ት/ማስፋፍያ፡ ይሆን፡ ዘንድ፡ ከልጆቻው፡ ጋር፡ ሆነው፡ እርዳታ፡ ባበረከቱበት፡ እለት፡፡
ክብር፡ እና፡ ምስጋና፡ ለዕውቀት ፡ አባት/እናቶቻችን ፤ ወላጆቻችን፡ እና፤ አስተማሪዎቻችን በሙሉ! በታላቁ፡ ንጉሠ፡ ነገሥታችን፤ ቀዳማዊ፡ ኃይለ፡ ሥላሴ፡ ዘመን፤ መምህራንን እና፡ ተማሪዎችን፡ ለማበረታታት ከላይ፡ ያለውን፡ ዓይነት: ማበረታቻ፡ ሜዳሊያ: ይሸልሙ፡ ነበር፡፡ እኛም፡ፈለጋቸውን/ምሳሌነታቸውን፤ ለቀጣዩ፡ትውልድ፡ለማውረስ፡ በቻልነው፡ መጠን፡ጥረት፡ እናደርጋለን፡፡
የኔ፡ ቁንዲ፤ጊዮርጊስ፤ ቦለድ፤ባለወልዴ፤
ደረፎ፤ማርያሜ፤ አንኮበር፤ ሲናዬ፤----፡
የሰማይ፡ ስር፡ አገር፤ ደመና፡ ለባሾች፤ ጠላ፡ እና፡ ጠጅ፡ ጮማ፤ ትህትና፤ አቅማሾች፤
ሐር፡አምባ፡እና፡ቆቦ፤ ፍቅሬ፡ግምብ፤ እመ፡ምህረት፤ ትዝታችሁ፡ያዘኝ፤ እንደ፡ወላጅ፡እናት፡፡
የወፍ፡ዋሻ፤ደኑ፤ዝናም፡እና፤ጉሙ፡የማይለው፤ ድንቅ፡አገራችንን፤ በታሪክ፤በውበት፤ያንቆጠቆጠው፤
የሲና፡ሚካኤል፤ የደረፎ፡ማርያም፤ የቦለድ፡ባለወልድ፤ የቁንዲው፡ጊዮርጊስ፤ እጹብ፡ ድንቅ፡ ነው፡፡
ቤተ፡ እሥራኤሎቹ፤ የሚኖሩባችሁ፤ ማስጫ፡ እና፡፤ ወፍ፡ ዋሻ፤ የኔ፡ አንኮበር፤ ሲና፤
ለናንተ፡የማይሆን፤ ምን፡ጉልበት፡ አለና ? ሁሌም፤ ልጎብኛችሁ፤ በጣይ፡ በደመና !!!
ታደሰ፡ ተገኝ፡ ሽታ፡፡ 20 ነሐሴ፤ 2016 ዓ/ም
ሰማእቱ፡ ቁንዲ፤ ቅዱስ፡ጊዮርጊስ፤ ትምህርት፡ቤታችንን፡ ከእግዚአብሔር፡ እና፡ ህዝባችን፡ ጋር፡ ይጠብቅልን !!!