loading

0%

PROJECT – IV      አራተኛው፤ መርሃ፡ ግብር፡፡


tadesse00000

  ባሌ፤ ክፍለ፡ ሃገር፤ አዳባ፡ ወረዳ፤ ለሰብስቤ፡ ዋሻ፤ እና፤ መስቀል፡ ደርኪና፡ አካባቢ፤ ቀበሌ፤ ገበሬዎች፡ መንደሮች፤ ህጻናት፤ ማዕከል፡ እንዲሆን፡ ታስቦ፡ ተጀምሮ፡ የነበረ፡፡

BALE PROVINCE; ADABA WOREDA; FOR SEBSIBE WASHA AND MESQEL DERKINA FARMING COMMUNITIES' CHILDREN፡


የመጀመርያው፡ እና፡ 2ኛው፡የአዳባ፡ ት/ጽ/ቤት፤ጉብኝት፡ታደለ፡ተፈራ፡እና፡ታደሰ፡ተገኝ፡ከት/ቢሮው፡መሪ፡ጋር

 1st visit to Bale's Adaba Education Office;  by Tadelle Tefera and Tadesse Tegegne.

በጋራ፡ ከት/ጽቤቱ፡ ጋር፡ ከተወያየን፡ እና፤ ሰብስቤ፡ ዋሻ፡ አጠገብ፡ ያለውን፡ የመስቀል፡ ደርኪና፡ የህጻናት፡  መዋያ፤ ሙሉ፡በሙሉ፡አፍርሰን፤ ወደ፡ ደረጃውን፡የጠበቀ፤ጠንካራ፡ መደበኛ፡የመ/ደ/ት/ቤትነት፡ ለመቀየር፡ በቃል፡ ከተስማማን፡ በኋላ፤ ሁለተኛውን፡ ቀጣይ፡ ጉብኝት፤ ፕሮፍ. አባራ፡ እና፡ ታደሰ፡ ተገኝ፡ አካሄዱ፡፡ፕሮፍ፡አበራ፡ገይድ፡ እና፡ ታደሰ፤ ከሞላ፡ጎደል፤ የከብቶች፡ ማደርያ፡የሚመስለውን፡ት/ቤት፡በጎበኙበት፡እለት፡ 

Day, when Prof. Abera Geyid (FB board member); and Tadese Tegegne; visited the shocking dilapidated structure that Adaba Woreda's; Sebsibe Washa and Mesqel Derkina children used to go to for schooling.



ባሌ፡ ክፍለ፡ ሃገር፡ በየዓመቱ፡ ከባድ፡ ዝናብ፡ ስለሚጥል፤ ብዙ፤ የገጠር፡ ት/ቤቶችም፡ ሆኑ፡ መኖርያ፡ ቤቶች፡ ግድግዳቸው፡በዝናብ፡እንዳይታጠብ፤ውጫቸው፡የሚሰራው፡በቀርቀሃ፡ነው፡፡ ስለዚህም፤የፈለገ፡ብርሃን፡ ማኅበር፤ ዓላማ፤ ት/ቤቱን፡በጠንካራ፤ ንፋስ/ብርድ፡በማያስገቡ፡ የግንባታ፡እቃዎች፡ በአዲስ፡መልክ፡ ለማሰራት፡ ነበር፡፡

ይህንኑ፡በአራተኛው፡ የፈብ፡ ጉዟችን፡ ከታደለ፡ ተፈራ፡ እና፡ ጌታቸው፡ ቅጣው፡ጋር፡ጎበኘተን፤ ለት/ቤቱ፡ለሌሎች፡ እንዳደረግነው፤ በመጀመርያ፤የመጸዳጃ፡ቤቶችን፡ እና፡ የንጹህ፡መጠጥ፡ውሃን፡በማሰራት፡እስተዋጽኦዋችንን፡ ለመጀመር፡የሶስትዮሽ፡የመርሃ፡ግብር፡ስምምነት፡ከወረዳው፡ ት/ቢሮ፡እና፡ ከገበሬዎቹ፡ተወካይ፡ጋር፡ ተፈራረምን፡፡

During our fourth visit to the school,  we signed a tripartite agreement, with the Adaba Woreda Education Office and Mesqel Derkina Community; to 1st construct a 6 rooms VIP latrine facility and a clean piped water supply system for the school and the community. 



ባሌ፡ ክፍለ፡ ሃገር፤ ምንም፡ እንኳ፤ ከፍተኛ፡ የውሃ፡ ሀብት፡ ቢኖረውም፤ ት/ቤቱም፡ ሆነ፤ በዙርየው፡ ያሉት፡ የገበሬዎች፡ማሕበረሰቦች፤ በዘመናዊ፡መልክ፡ጎልብቶ፤ በቧንቧ፡ተስቦ፡የደረሰለት፡ንጹህ፡የመጠጥ፡ውሃ፡ አቅርቦት፡ የለውም፡ ነበር፡፡ አዲሱን፡ ት/ቤት፡ ለመስራትም፡ ሆነ፤ ለህጻናቱም፤ ለመምህራኑም፡ እና ለማሕበረሰቦቹም፤ የመጠጥ፡ውሃን፡እና፡ መጸዳጃ፡ቤትን፡ እውን፡ማድረግ፤ የመጀመርያው፡ ስራችን፡ አድርገን፡ ነበር፡የጀመርነው፡፡


ፎቶ፡ 1፡ ከት/ቤቱ፡ አምስት፡መቶ፤ሜትር፡ያህል፡ በስተ፡ሰሜን፡ተራራ፡ስር፡ምንጭ፡ ስላገኘን፤ለውሃው፡የመርሃ፡ ግብራችን፡አንዱ፡አካል፡በማድረግ፤ከወረዳው፡ት/ጽ/ቤት፡እና፡ የሰብስቤ፡ዋሻ፡እና፡መስቀል፡ደርኪና፡ህዝብ፡ተወካይ፡ጋር፡የሶስትዮሽ፡ውል፡በመፈራረም፤ስራ፡ተቋራጮችን፡አወዳድረን፡ ለአሸናፊው፡ለመስጠት፡ ስራ፡ ጀምረን፡ ነበር፡፡ 

ፎቶ፡ 2፡ ምንጩ፡ከሚገኝበት፡ስፍራ፡በስተደቡብ፡ ጽዶች፡ መሃል፡  የሚገኘው፤የት/ቤቱ፡እይታ ፡፡


ለተማሪዎች፡ ነጻ፡ የትምህርት፡ ጽ/መሳርዎችን፡ እና፡ የደንብ፡ልብሶችን፡እደላም፡ጀምረን፡ነበር፡፡

We also issued 1st round supplies of Free FB school uniforms & stationary items to the school and children.



እንደ፡መጀመርያው፡የእንጦጦው፡መርሃ፡ግብር፤ማለቅያው፡ያላማረው፤4ኛው፡መርሃ፡ ግብር፡ 

TRAGIC END OF THIS  4th PROJECT,  LIKE THAT OF OUR 1st PROJECT AT ENTOTO St. Raguel/Elias.


ይህን፡ እየሰራን፤ እያለን፤ እና፤ አጠቃላይ፡ መርሃ፡ ግብሩን፡ በመቅረፅ፤ ከወረዳው፡ ትምህርት፡ ጽህፈት፡ ቤት፡ እና፡ ከተረጂው፡ ማኅበረሰብ፡ ጋር፡ ትልቁን፡ የት/ቤቱን፡ ህንጻ፡ ግንባታ፡ ለማስጀመር፤ የሶስትየትዮሽ፡ የመርሃ፡ ግብር፡ ስምምነት፤ ለመፈራረም፡ እየተቃረብን፡ ባለንበት፤ ወቅት፤ በወረዳው፤ የኦሮሞ፡ እስልምና፡ እና፡ የዘር፡ አክራሪዎች፤  ክርስትያኖችን፡ መግደል፡ እና፤ ቤተ፡ ክርስትያንን፡ ማጥቃት/ማጥፋት፡ ጀመሩ፡፡ የእንጦጦው፡ራጉኤል/ኤልያስ፡ፈብ፡ ት/ቤታችን፡በሱሉልታ፡ወረዳ፡ ኦሮሞ፡ባለስልጣኖች፤በወያኔ፡ አበረታችነት፡ሲዘረፍ/ ሲወድም፤ ባሌ፡ ክ/ሀ ይሻለን፡ ይሆናል፡ ብለን፡ ነበር፡ አዝያ፡የጀመርነው፡፡ ነገር፡ግን፡ የባሰ፡ሆኖ፡አገኘነው፡፡ ለተፈጸመው፡ፋሽስታዊው፡ወንጀልም፤ ከመንግሥት፡ ምንም፡ የማውገዝም፡ ሆነ፡የማረም፡ እርምጃ፡ ሲወሰድ፡ ስላላየን፤ መላው፡የፈብ፡ ሥራ፡አስፈጻሚ፡ አባላት፤ እዚህ፡ አካባቢ፡ ከዛሬ፡ ጀምሮ፡ በጭራሽ፡ ላንመለስ፡ ወስነን፤ መርሃ፡ግብሩን፤ ሰርዘን፡ ወጥተናል፡፡ 

While eagerly waiting to sign the main Project agreement and launch a bid for the construction of 6 rooms VIP latrines and Clean School water supply system; and the main school building / class rooms;  radical Islamists / ethnicists, started brutally killing Christians and attacking churches in the Woreda, with absolute impunity.  During that time;  similar crimes took place in towns between  Bale/Adaba and Addis Abeba; driving via Addis Awassa road. Christian and none Oromo dwellers of towns like  Ziway and Shashemene  were attacked brutally.  Since we even failed to hear condemnation of the act  by  Government; we officially declared cancellation of  our plan  to realize a Free FB School Project in  Adaba Woreda (Bale Province), and withdrew from the area indefinitely.