loading

0%

PROJECT – V      አምስተኛው፤ መርሃ፡ ግብር፡፡

  tadesse00000

ሰሜን፡ ሸዋ፤ ተጉለት፡ ወረዳ፤ ጣርማ፡ በር፡አጠገብ፤ 

ለአንዲት፡ ጥድ፤ ለገነት፡ዋሻ፡ማርያም፡ እና፡ ንፋስ፡ ምድር፡አማኑኤል፡ ቀበሌዎች፤ ህጻናት፤ ማዕከል፡ እንዲሆን፡ ታስቦ፡ የተጀመረ፡፡


NORTH SHEWA;  TEGULET WOREDA;  AT  ADDISGE (NEAR  T'ARMA BER)

FOR ANDIT T'ID;  GENET WASHA AND NEFAS MIDIR FARMING COMMUINITIES:



አምስተኛው፡ መርሃ፡ ግብር፡ የተጀመረው፡ በተጉለት፡ እና፤ ቡልጋ፡ አውራጃ፤ ተጉለት፡ ወረዳ፤ አዲስጌ፡ ቀበሌ፤ አንዲት፡ ጥድን ት/ቤትን፡ ማእከል፡ በማድረግ፤ ለአንዲት፡ ጥድ፤ ለገነት፡ዋሻ፡ማርያም፤ እና፡ ለንፋስ፡ምድር፡አማኑኤል፡ ገበሬዎች፡መኖርያ፡አካባቢ፡ላሉ፡ህጻናት፡ ታስቦ፡ የተጀመረ፡ ነው፡፡ ይህም፤ ባሌ፡ ክ/ሃገር፡ ልናውለው፡ የነበረውን፡ አቅማችነን/እቅዳችንን፤ በአክራሪ፡እስልምና፡ተከታዮች፡እና፡ዘረኞች፡ጥቃት፡ምክንያት፡ስላቋረጥን፡ እና፤ እኛ፤ ለህይወታችን፡ በመስጋት፡ ለቀን፡ስለወጣን፡ የነበረንን፡አቅም፡በዚህ፡አንፃራዊ፡ሰላም፡ባለበት፡በማዛወር፡ አዝተዋጽኦዋችንን፡ለማበርከት፡ነው፡፡  


እላይ፤ ፎቶ፡ 1፡ የወረዳው፡ ትምህርት፡ ቢሮ፡ ኃላፊ፡ አቶ አፈወርቅ፡ ዘውዴ፤  የፈብ፡ አባላትን፡ በተዋወቁበት፡ እለት፡፡

     ፎቶ፡ 2፡ የወረዳው፡የት/ቢሮ፡ኃላፊ፤ የመጀመርያውን፡ጉብኝት፤ካደረገው፤ የፈለገ፡በብርሃን፡ማኅበር፡አባላት፤ጋር        ከግራ፡ወደ፡ቀኝ፤ታደሰ፡ተገኝ፤ወ/ሮ፡ስንዱ፡ብሥራት፤ወ/ሮ፡ገነተ፡ጣሰው፤እና፡ዳር፤ላይ(5ኛው)አቶ፡ታደለ፡ተፈራ፡፡



  ከዝያም፡ አዲስጌ፡ ቀበሌ፡ በመሄድ፡ አማራጭ፤ አንዲት፡ ጥድ፡ መሠረታዊ፡ የመ/ደ/ትቤትን፡ እላይ፡ የመጀመርያው፡ እና፡ 2ኛው፡ ፎቶዎች፡ ላይ፡ እንዳለው፤ በት/ቤቱ፤ ር/መምህር፡ እና፡ መምህራኑ፤ አስጎብኝነት፡ተመለከትን፡፡  ፎቶ፡ 2፡ ወ/ሮ፡ ስንዱ፡ ብሥራት፡ እና፡ ወ/ሮ፡ ገነት፡ ጣሰው፤ እኛም፤ ተማሪዎቹን፤በየክፍላቸው፡ገብተን፡አበረታታን፡፡ ታላቁ፡ንጉሠ፡ነገሥታችን፡ ቀ.ኃ.ሥ፤በአንዳንድ፡ ት/ቤቶች፡  እየሄዱ፡ተማሪዎችን፡ያበረታቱ፡እንደነበር፡(ፎቶ፡3)አስታውሰን፤ደስ፡አለን፡፡ቀጥሎም፡ይዘናቸው፡ የሄድነውን፡ የጽህፈት፡መሳርያዎች፡ ለተማሪዎቹ፤ለመምህራኑ፡ እና፡ ለትምህርት፡ቤቱ፡ ለገስን/አደልን፡፡


 ከዝያም፤ ት/ቤቱን፡ ደረጃውን፡  ያሟላ፡ እንዲሆን፡ ምን፡ ምን፡ መርዳት፡እንዳለብን፡ በማለት፤መምህራኑን፡   ስንጠይቅ፤መምህራኑ፤በአንድ፡ቃል፡"ከረዳችሁን፤መጀመርያ፡ንጹሕ፡የመጠጥ፡ውሃ፡አስገቡልን"፤በማለት፤ ተማጸኑን፡፡ የውሃ፡አቅርቦት፤በቅርቡ፡ካልተረጋገጠላቸው፡ት/ቤቱን፡ለቀው፡ለመሄድ፡እያሰቡ፡እንደነበርም፤ነገሩን፡፡ 

እኛም፤ ጥያቄያቸውን፡ በመቀበል፡ ለወረዳው፡ ት/ጽ/ቤት፡ እና፡ ለአንዲት፡ ጥድ፡ ት/ቤት፡  ለውሃ፡ ስራው፡ በአካባቢው፡ 

 ያሉ፡ምንጮችን፡በማጥናት፤በአውራጃው፡ ካሉ፡ የውሃ፡ ሥራ፡ ባለሙዎች፡ውስጥ፡ በጨረታ፡ ተወዳድሮ፡ የሚመረጠው፤ 

 ምንጩን፡ አጎልብቶ፤ እስከ፡ ት/ቤቱ፡ በቧንቧ፡ በመሳብ፡ በባለ፡ ሁለት፡ ጡት፡ ማከፋፈያ፡ ተሰርቶ፤ ለት/ቤቱም፡ ሆነ፡ 

 በዙርያው፡ ለሚኖሩ፡ የገበሬ፡ ቤተሰቦች፡ እንዲቀርብ፡ በፈለገ፡ ብርሃን፡ ማኅበር፡ስም፡ ጨረታ፡እንዲያወጡልን፡ እና፡ 

 የሚቀርቡትን፡ የተወዳዳሪዎች፡ ጨረታ፡ሰነዶቹን፡እንዲልለኩልን፡አሳሰብን፡፡ 

 የወረዳው፡ት/ቢሮም፤ከወረዳው፡ውሃ፡ስራዎች፡ቢሮ፡ጋር፡በመተባበር፤ጨረታ፡አውጥተው፡ሰነዶቹን፡አዲስ፡ አበባ፡ ላኩልን፡፡ 

 የፈብ፡ስራ፡አስፈፃሚ፡ቡድንም፡ከገመገመ፡በኋላ፡ አንዱን፡መርጦ፡ለመፈራረም፡ ወደ፡ደ/ብርሃን፡ት/ቢሮ፡ቀጠሮ፡ ይዘን፡ሄድን፡፡


 በእለቱም፡ አብረን፡ የተጓዝነው፡ ከውጭ፡ ሃገር፡ ኑሮው፤ ተመልሶ፡ የነበረው፤ የጀነራል፡ ዊንገት፡ ት/ቤት፡ ወንድማችን፡ 

 ክብረት፡ ሱራፌል፤ ታደለ፡ ተፈራ፡ እና፡ እኔ (ታደሰ፡ተገኝ)፡ ነበርን፡፡ ለአንዲት፡ጥድ፡ ት/ቤት፡ የንጹሕ፡ የመጠጥ፡ ውሃ፡ 

 አቅርቦት፡ ስራም፡ ፈለገ፡ ብርሃንን፡ በመወከል፡ ክብረት፡ ሱራፌል፤ ከጨረታው፡ አሸናፊ፡ የስራው፡ ተቋራጭ፡ እና፡ 

 ከወረዳው፡ ውሃ፡ስራዎች፡ጽ/ቤት፡ እና፡ ትምህርት፡ጽ/ቤትም፡ ኃላፊዎች፡ጋር፡በመፈራረም፤ተቋራጩ፤ አስፈላጊውን፡

 ግብአት፡ሁሉ፡ አቅርቦ፡ ስራውን፤ ቢበዛ፡ በሁለት፡ወራት፡ ጨርሶ፡ ሊያስረክበን፡ ተፈራረምን፡፡ 


ፎቶ 1፡ የፈለገ፡ ብርሃን፡ አባል፤ ወንድማችን፤ ክብረት፡ ሱራፌል፤ ውሉን፡ ፈለገ፡ ብርሃንን፡በመወከል፡ ሲፈርም፡፡

ፎቶ፡ 2፡ ከፊርማው፡በኋላ፤ት/ቢሮው፡በር፡ላይ፤ ክብረት፡እና፡እኔ፤ ከስራ፡ተቋራጩ፤እና፡  ት/ቢሮው፡ሃላፊዎች፡ጋር፡፡

በተስማማነውም፡ መሰረት፡ ተቋራጩ፡ ስራውን፡ በሁለት ወራት፡ ተኩል፡ ውስጥ፤ በህብረተሰቡ፡ የጉልበት፡ አስተዋጽኦም፡ ጭምር፤ በሚገባ፡ጨርሶ፤እንድንረከበው፡ ጠራን፡፡ እኛም፡ ከወረዳው፡ ውሃ፡ስራዎች፡ጽ/ቤት፡ኃላፊ፡ ጋር፡ በመጓዝ፡ ተረከብን / መረቅን፡፡ ህፃናቱም / መምህራኑም፤ የአካባበውም፡ ገበሬዎችም / ነዋሪዎችም፤ ማሕበረሰብም፤ እጅግ፡ ተደሰቱ፡፡




ፈለገ፡ ብርሃን፡ ማኅበርንም፡ ለማመስገን፤ መምህራኑ፡ እና፡ የአካባቢው፡ ነዋሪዎች፡ ገበሬዎች፡ ቤተሰቦች፤  ምሳ፡ ጋበዙን፡፡  በአገሩ፡ ባህልም፤ ልክ፤ አንኮበሬዎች፡ ቁንዲ፡ ላይ፤ እንዳደረጉልን፤ ተጉለቴዎችም፡ በጣም፡ ጥልቅ፡ ቡሉኮ፡ ሸለሙን፡፡ አመስግነንም፡ ተቀበልን፡፡




የፈለገ፡ ብርሃን፡ አባላት፤ አቶ፡ ንጉሤ፡ ቁምላቸው፤ ወ/ሮ፡ አስቴር፡ ሣህሉ፡ እና፤ ታደሰ፡ ተገኝ፤  የአንዲት፡ ጥድ፤ ት/ቤትን፡ በጎበኘንበት፡ እና፡ ለገነት፡ ዋሻ፡ ማርያም፤ ለንፋስ፡ ምድር፡ አማኑኤል፡ እና፤ ለአንዲት፡ ጥድ፡ ት/ቤቶች፡ ተማሪዎች፡ የጽ/መሣርያዎች (ደብተር፤ እርሳስ፡ እስክሪፕቶ፡ እርዳታን፡ ባከፋፈልንበት፡ ቀን፡፡


ከዝያም፡ የወረዳውን፡ ት/ጽቤት፤ የግንባታ፡ ክፍል፡ ሃላፊ፡ መሃንዲስ፡ የተባለውን፡ አቶ፡ ፍጹምን፡ "ከዚህ፡ ቀጥሎ፡ ያለው፡ እቅዳችን፡ ት/ቤቱ፡ አሁን፡ ያለበት፡ የመሬት፡ ስፋት፤ አነስተኛ፡ ስለሆነ፤ ብዙ፡ ቦታ፡ የማይወስድ፤ ባለስምንት፡ ክፍሎች፤ አዲስ፡ አበባ፡ ውስጥ፡ እንዳሉት፡ አይነት፤ ባለ፡ አንድ፡ ፎቅ፡ (ከላይ፡ አራት፡ እና፡ ምድር፡ ላይ፡ አራት) ክፍሎች፡ ያላውን፡ የመማርያ፡ ህንጻ፡ እና፡ በለ፡ ስድስት፡ ክፍሎች፡ ዘመናዊ፡ መጸዳጃ፡ ቤትን፡ ማሰራት፡ ስለሆነ፤ ልክ፡ እንደ፡ ውሃው፡ ስራ፡ እንደተባበራችሁን፤ ለዚህም፡ ጨረታ፡ አብረን፡ እንድናወጣ፡ ተባበሩን" ብለን፤ ስንጠይቅ፤ የመለሰልን፤ " እስካሁን፡ እንግዶች፡ ናችሁ፡ ብለን፡ ለት/ቤቱ፡ የቧንቧ፡ ውሃ፡ ስታሰሩ፡ ተባብረናችኋል፡፡ ከእንግዲህ፡ ለኛ፡ ማማከር / መተባበር፡ ተገቢውን፡ ክፍያ፡ እስካልከፈላችሁን፤ ምንም፡ ልንፈቅድ፡ አንችልም" የሚል፡ ነበር፡፡ ይህንኑ፤ ለወረዳው፡ ት/ጽ/ቤት፡ ሃላፊም፡ አሳውቀን፡ እስካሁን፡ መልስ፡ አየጠበቅን፡ እንገኛለን፡፡

በዚህ፡ ሁኔታ፡ ላይ፡ እያለን፡ የሀገራችን፡ ጸጥታ፡ በጣም፡ እየተበላሸ፡ ስለመጣ፤ እና፤ ከአዲስ፡ አባባ፡ መውጣትም፡ ሆነ፡ ወደ፡ አዲስ፡አበባ፡ መግባት፡ እየከበደ፡ስለሄደ፤ ማንኛውንም፡ ወደ፡ ፈለገ፡ ብርሃን፡ ገጠር፡ት/ቤቶቻችን፡ የሚደረግ፡ እንቅስቃሴን፡ በአጠቃላይ፡አቁመን፡ የሰላምን፡ መምጣት፡ እየተጠባበቅን፤እንገኛለን፡፡ 


የፈለገ፡ ብርሃን፡ አባላት፤ ኢንጅ፡ ለማ፡ ተ/ሃይማኖት፤ አቶ፤ አክሊሉ፡ ዘውዴ፤ አቶ፡ ታደለ፡ ተፈራ፡ እና፡ ታደሰ፡ ተገኝ፤ አንዲት፡ ጥድ፤ ት/ቤትን፡ በጎበኘንበት፡ እና፡ ለገነት፡ ዋሻ፡ ማርያምም፤ ለንፋስ፡ ምድር፡ አማኑኤልም፡ ተማሪዎች፡ የጽ/መሣርያዎች (ደብተር፤ እርሳስ፡ እስክሪፕቶ) እና፡ የመጻህፍት፡ እርዳታን፡ ባከፋፈልንበት፡ ቀን፡፡